የሀገር ውስጥ የንግድ ምልክት ምዝገባ ማመልከቻ መስፈርቶች
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከደጋፊ ደብዳቤ ጋር
- የንግድ ምልክት ምዝገባ ማመልከቻው በተወካይ አማካኝነት የሚቀርብ ከሆነ፣ የውክልና ደብዳቤ መቅረብ አለበት፣
- የንግድ ምልክቱ ናሙና፦ አንድ (1) ትልቅ መጠን በኤ-4 ወረቀት እና ስምንት (8) አነስተኛ መጠኖች በኤ-4 ወረቀት፣
- የማመልከቻ ቅጽ በሁለት (2) ቅጅ መሙላት፣
- የማመልከቻ ክፍያ ለአንድ ምድብ 1750 ብር ሲሆን፣ የንግድ ምልክቱ ከአንድ በላይ የዕቃዎች ወይም የአገልግሎቶች ምድብ የሚያጠቃልል ከሆነ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ምድብ የ1750.00 ብር 50% ተጨማሪ ክፍያ ይጨምራል፣
- የምስክር ወረቀት (የምዝገባ) ክፍያ ለአንድ ምድብ 3000.00 ብር ነው፣
የውጭ አገር የንግድ ምልክት ምዝገባ ማመልከቻ መስፈርቶች
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም የውጭ ሀገር የንግድ ምልክት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም የንግድ ድርጅቱ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት ምስክር ወረቀት፣
- የንግድ ምልክት ምዝገባ ማመልከቻው በተወካይ አማካኝነት የሚቀርብ ከሆነ፣ ሕጋዊነቱ የተረጋገጠ የውክልና ሥልጣን ማረጋገጫ ሰነድ አብሮ መቅረብ አለበት፣
- የንግድ ምልክቱ ናሙና፦ አንድ (1) ትልቅ መጠን በኤ-4 ወረቀት እና ስምንት (8) አነስተኛ መጠን በኤ-4 ወረቀት፣