ለምዝገባ የሚያመለክት ድርጅት ወይም ተቋም የሚከተሉትን ማቅረብ አለበት
- የተሞላ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ማመልከቻ ቅጽ
- የደራሲው ዝርዝር መረጃ (ከድርጅቱ የተለየ ከሆነ)
- የመብት ማረጋገጫ ሰነድ፡ የሥራ ድርሻ፣ የሥራ ውል፣ ወይም የባለቤትነት ዝውውር ስምምነት
- የሥራው ቅጂ (በዲጂታል እና/ወይም ሃርድ ኮፒ)
- የምዝገባ ክፍያ የከፈሉበት ማስረጃ
- የውክልና ስልጣን ሰነድ (በተወካይ አማካኝነት የሚቀርብ ከሆነ)
- የፈቃድ ማስረጃ (ለምሳሌ፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ ወይም የድርጅት መመስረቻ ምስክር ወረቀት)
- የአመልካች ቃለ መሃላ፡ አመልካቹ የሥራው ባለቤት መሆኑን በቃለ መሃላ ማረጋገጥ አለበት
ለቅጅ መብት ምዝገባ የሚያመለክት ግለሰብ የሚከተሉትን ማቅረብ አለበት፣
- የተሞላ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ማመልከቻ ቅጽ
- የደራሲው መረጃ (ከአመልካቹ የተለየ ከሆነ)
- የሥራው ቅጂ (በዲጂታል እና/ወይም ሃርድ ኮፒ)
- የምዝገባ ክፍያ የከፈሉበት ማስረጃ
- የውክልና ስልጣን ሰነድ (በተወካይ አማካኝነት የሚቀርብ ከሆነ)
- የአመልካች ቃለ መሃላ፡ አመልካቹ የሥራው ባለቤት መሆኑን በቃለ መሃላ ማረጋገጥ አለበት